Fana: At a Speed of Life!

ከአንድ እናት ሆድ ውስጥ 28 ኪሎ ግራም የሚመዝን እጢ ወጣ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዲላ ከተማ በሚገኘው ሰላም ሆስፒታል በተደረገ የቀዶ ጥገና ህክምና ከአንድ እናት ሆድ ውስጥ 28 ኪሎ ግራም የሚመዝን እጢ መውጣቱ ተሰምቷል፡፡

ከምዕራብ ጉጂ ዞን ሃሚባላ ዋማና ወረዳ ጮርሶ ጎሊጃ ቀበሌ በመምጣት በሰላም ሆስፒታል የህክምና ክትትል ሲያደርጉ የቆዩት የ48 አመት እናት ወይዘሮ አበሩ አላኮ በተደረገላቸው የቀዶ ጥገና ህክምና 28 ኪሎ ግራም የሚመዝን እጢ ከሆዳቸው ውስጥ መውጣቱን የማህጸንና ጽንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ጌታቸው መርጊያ ተናግረዋል፡፡

ቀዶ ጥገናው 3 ሰዓታት የወሰደ መሆኑን የጠቀሱት ዶክተር ጌታቸው በአሁኑ ሰዓት ወይዘሮ አበሩ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ መግለጻቸውን ከጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.