ፋና ስብስብ

ከአንድ እናት ሆድ ውስጥ 28 ኪሎ ግራም የሚመዝን እጢ ወጣ

By Feven Bishaw

March 02, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዲላ ከተማ በሚገኘው ሰላም ሆስፒታል በተደረገ የቀዶ ጥገና ህክምና ከአንድ እናት ሆድ ውስጥ 28 ኪሎ ግራም የሚመዝን እጢ መውጣቱ ተሰምቷል፡፡

ከምዕራብ ጉጂ ዞን ሃሚባላ ዋማና ወረዳ ጮርሶ ጎሊጃ ቀበሌ በመምጣት በሰላም ሆስፒታል የህክምና ክትትል ሲያደርጉ የቆዩት የ48 አመት እናት ወይዘሮ አበሩ አላኮ በተደረገላቸው የቀዶ ጥገና ህክምና 28 ኪሎ ግራም የሚመዝን እጢ ከሆዳቸው ውስጥ መውጣቱን የማህጸንና ጽንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ጌታቸው መርጊያ ተናግረዋል፡፡