የክተት አዋጅ በታወጀባት ወረኢሉ ከተማ 126ኛው የዓድዋ ድል በዓል ተከበረ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዳግማዊ አፄ ሚኒልክ የክተት አዋጅ ባወጁባት ወረኢሉ ከተማ 126ኛው የዓድዋ ድል በዓል በድምቀት ተከብሯል።
በድል በዓሉ ላይ የተገኙት በመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ዋና ሀላፊ ሜጀር ጀኔራል አህመድ ሀምዛ፥ የኢትዮጵያውያን ጠንካራ የአንድነት መንፈስ ማሳያ፣ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ውል የሆነው ዓድዋ የአንድነታችን እንጅ የልዩነታችን ምክንያት ሊሆን አይገባም ብለዋል።
የደቡብ ወሎ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተስፋ ዳኜ በበኩላቸው የዓድዋ ድል በዓልን በወረኢሉ ከተማ ከአሁኑ በተሻለ ለማክበር በቀጣይ ብዙ ስራ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።
ወረኢሉ ከዓድዋ ድል ጋር የተያያዙ በርካታ ቅርሶችና ቦታዋች ያሉባት ከተማ እንደመሆኗ ቅርሶቹን ጠብቆ ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍ ይገባልም ነው ያሉት።
በበዓሉ ላይ የፌደራል እና የክልል አመራሮች እንዲሁም በደቡብ ወሎ ዞን ምዕራብ ወረዳዋች የባህል ቡድኖች ታድመዋል ።
በኢሳያስ ገላው
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!