የሀገር ውስጥ ዜና

ዶክተር ጌዲዮን ከተመድ ሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጋር ተወያዩ

By Alemayehu Geremew

March 02, 2022

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፍትህ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ከተመድ ሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባችሌት ጋር ተወያዩ።

ሚኒስትሩ በ49ኛው የተመድ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ እየተሳተፉ ይገኛል።

ከስብሰባው ጎን ለጎን በነበራቸው ውይይትም በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት አያያዝን በተመለከተ ገለጻ ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ከዚህ ባለፈም በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶችን አያያዝ ለመከታተል በተቋቋመው የሚኒስትሮች ግብረ ሃይል ተግባራት ዙሪያ ገለጻ አድርገውላቸዋል።