Fana: At a Speed of Life!

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 3ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ ዓመት 50ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ፡፡
 
ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት በሚያካሂደው ጉባዔ የተለያዩ አስፈፃሚ አካላት የስድስት ወራት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርትን ይገመግማል ተብሏል።
 
በጉባዔው ምክር ቤቱ በ3ኛ የሥራ ዘመን አንደኛ ዓመት 7ኛ አስቸኳይ ጉባዔ ቃለ-ጉባዔ ተወያይቶ ያፀድቃልም ተብሎ ይጠበቃል።
 
በተጨማሪም የአስተዳደሩ አስፈፃሚ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የ2014 ዓ.ም የመጀመሪያ የ6 ወራት አፈፃፀምን ይገመግማልም ተብሏል።
 
በቀረበው ሪፖርት ላይ የቋሚ ኮሚቴዎች አስተያየት ተሰጥቶበት አዳዲስ ሹመቶችን በማፅደቅ ጉባዔው እንደሚጠናቀቅም ይጠበቃል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.