Fana: At a Speed of Life!

የሩስያ ወታደራዊ ኃይል የዩክሬኗን ኬርሰን ከተማ ተቆጣጠረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የሩስያ ኃይል በሰባተኛ ቀኑ ወታደራዊ ዘመቻ በደቡብ ዩክሬን የምትገኘውን ኬርሰን ከተማ መቆጣጠሩን አስታውቋል፡፡
የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እንዳስታወቀው፥ የሩስያ ጦር በጥቁር ባህር አካባቢ የምትገኘውን የኢኮኖሚ ማዕከልና የኬርሰን ኦብላስት ግዛት ዋና ከተማ የሆነችውን ኬርሰንን ከሰዓታት በፊት መቆጣጠሩን አር ቲ የዜና ምንጭ ዘግቧል፡፡
ከክሬሚያ በስተሰሜን አቅጣጫ የምትገኘው እና ሩብ ሚሊየን የሚጠጋ ህዝብ ያላት ኬርሰን ከተማ እስካሁን በሩስያ ጦር እጅ የወደቀ ትልቋ ከተማ መሆኗ ነው የተገለፀው።
የከተማዋ ከንቲባ ኢጎር ኮላይካዬቭ ቀደም ሲል እንደተናገሩት፥ የሩስያ ወታደራዊ ኃይሎች የኬርሰንን ባቡር ጣቢያ እና ወደብ ለቀናት በተካሄደ ውጊያ በቁጥጥር ስር በቁጥጥራቸው ስር አድርገዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.