Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ መንግስት እየወሰዳቸው ያለው እርምጃዎች በሀገሪቱ ውጥረትን ለማርገብ የሚያስችሉ ናቸው – ቻይና

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ መንግስት እየተወሰዱ ያሉ የተለያዩ እርምጃዎች በሀገሪቱ በተለይም በሰሜናዊ ክፍል ያለውን ውጥረት ለማርገብ አወንታዊ ሚና ሊጫወቱ የሚችሉ መሆናቸውን ቻይና ገለፀች።
 
የቻይና የውጭ የሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌን ቢን እንደተናገሩት፥ የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል የነበረውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት ታውጆ የቆየውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከማብቂያ ቀደም ብሎ ማንሳቱን እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊት ወደ ትግራይ ክልል ዘልቆ እንዳይገባ ማድጉን ቻይና በአወንታ ትመለከታለች።
 
እንደዚሁም ሀገራዊ ምክክር ለማድረግ የሚያስችል መደላድል ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን ቻይና መመልከቷን ነው ቃል አቀባዩ ያነሱት።
 
እነዚህ የመንግስት እርምጃዎች በሀገሪቱ በተለይም በሰሜናዊ ክፍል ያለውን ውጥረት ለማርገብ አወንታዊ ሚና እንደሚጫወቱ ገልፀዋል።
 
ቻይና የኢትዮጵያ ህዝብ ቅን ወዳጅ መሆኗን ያወሱት ቃል አቀባዩ፥ የሚመለከታቸው አካላት ልዩነቶችን በውይይትና በድርድር በመፍታት አገሪቷን ወደ ሰላም እና ልማት ለማምጣት በቅንጅት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
 
በዚህ ረገድ ቤጂንግ አስፈላጊውን ትብብር ለማድርግ እና ቁርጠኛ መሆኗን ነው ዋንግ ዌን ቢን ያረጋገጡት።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.