የሶማሌ ክልል መንግስት ለድርቅ አደጋ መከላከያ የሚውል ተጨማሪ 40 ሚሊየን ብር በጀት መደበ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል መንግስት ለድርቅ አደጋ መከላከያ የሚውል ተጨማሪ 40 ሚሊየን ብር በጀት መመደቡን አስታውቋል፡፡
በሶማሌ ክልል ርዕሰ መሰተዳድር አቶ ሙሰጠፌ ሙሃመድ የሚመራ የድርቅ ምላሽ ዓብይ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት በርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዷል፡፡
በዚህም በተፈጥሮ ድርቅ አደጋ ለተጎዱት ማህበረሰብ ለውሃና ለምግብ የሚውል ተጨማሪ 40 ሚሊየን ብር እንደሚመደብ መወሰኑ ነው የተገለጸው፡፡
የተመደበው ብር የውሃ ማጓጓዣ፣ የዕለት ደራሽ ምግቦች፣ መድሃኒት እና ለእናቶች የሚሆን የተለያዩ የተመጣጠነ ምግቦች መግዣ የሚውል መሆኑን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ለድርቁ ምላሽ ለመስጠት እስካሁን የክልሉ መንግሥት ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ በመመደብ የተለያዩ ርብርቦችን በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ተመላክቷል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!