Fana: At a Speed of Life!

ዳያስፖራው በአገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ያለውን ተሳትፎ የበለጠ ማጠናከር ይገባል-አምባሳደር ብርቱካን አያኖ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአገረ መንግስት ግንባታ ሂደት የዳያስፖራ ማህበረሰቡን ተሳትፎ ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ተናገሩ።
 
ለአዲስ ተሾሚ አምባሳደሮች እየተሰጠ በሚገኘው ስልጠና የኢትየጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ ከኤምባሲዎች ጋር ስለሚኖረው ግንኙነት በተመለከተ ገለጻ ተደርጓል።
 
አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በአገረ መንግስት ግንባታ ሂደት በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ዘርፍ የዳስፖራውን ተሳትፎ የበለጠ ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
 
ለኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሁለቱም መስክ ተሳትፏቸው እንዲጎለብት ባለፉት ዓመታት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውንያስታወሱት አምባሳደር ብርቱካን ፥ ዳያስፖራው አገሩን በሚጠቅምበት ሁኔታ ማገዝ ከአምባሳደሮች ይጠበቃል ብለዋል።
 
ከዚህ ባለፈም በሁሉም የውጭ ግንኙነት ስራ እንዲሳተፉ ማበረታታት እንዲሁም አገልግሎቶች ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን መስራት ይገባል ሲሉም አጽንዖት ሰጥተዋል።
 
የዳያስፖራ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሀመድ እንድሪስ በበኩላቸው፥አምባሳደሮች በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን መብትና ጥቅም ማስጠበቅ፣ የኢንቨስትመንት፣ የንግድና ቱሪዝም ተሳትፎን ማጐልበት እና የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ማሳደግ ተሳትፎን ማጠናከር እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡
 
እንዲሁም ባህላዊ ዕሴቶችን ማዳበር እና ገፅታ ግንባታ ማሳደግ፣ በዲሞክራሲያዊ ሂደት የሚኖረውን ተሳትፎ ማሳደግ እና የግብረ ሰናይና የልማት ማህበራት ያለውን ተሳትፎ ማጠናከር ይገባል ብለዋል።
 
በአገራዊ ጉዳዮች ወቅታዊ ተልዕኮዎች፣ በአገራዊ ፕሮጀክቶች በብሄራዊ ጥቅም ማስከበር እንዲሁም በአረጓዴ ልማት ዘርፎች በስፋት እንዲሳተፉ አዲስ አምባሳደሮች ከበፊቱ በላቀ ሁኔታ መስራት እንደሚገባቸው መመላከቱንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.