Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ሚኒስትሩና የአማራ ክልል ርዕሠ መስተዳድር በዘንዘልማ ቀበሌ የለማ የስንዴ ማሳን ጎበኙ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስትር ዑመር ሁሴን  እና የአማራ ክልል ርዕሠ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በባህርዳር ከተማ አስተዳደር ዘንዘልማ ቀበሌ የለማ የስንዴ ማሳን ጎብኝተዋል፡፡

ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ወቅት እንደገለፁት÷ በክልሉ ለበጋ መስኖ ልማት አመቺ የሆነ ሰፊ መሬት እንዳለ በመጠቆም በአሁኑ ሰዓት የለማው የበጋ ስንዴ ከፍተኛ ምርት የሚሰጥ ነው ብለዋል።

እንደ ሀገር 400 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ ስንዴ ለማምረት እንደታቀደ ገልጸው÷ በመጀመሪያው ዙር ብቻ ከ450 ሺህ ሄክታር በላይ በመሸፈን ከእቅድ በላይ መከወን ተችሏልም ብለዋል፡፡

በአማራ ክልል በጦርነት የተጎዳውን ምርት ለመተካት ምክንያት ተደርጎ እየለማ ያለው የበጋ ስንዴ የሚበረታታ መሆኑንም ተናግረዋል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በበኩላቸው÷ ይህ የሙከራ ውጤት በአመት ሶስት ጊዜ ማምረትና የአርሶአደሩን ህይወት መለወጥ እንደሚቻል አመላካች  መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አርሶአደሩ ድህነትን በመዋጋት ይህንን መሰል ምርት ማቅረብ ከቻለ ግብዓት ተጠቃሚ ፋብሪካዎች እንዲቋቋሙ የስራ እድል እንዲፈጠርም ያስችላል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በክልሉ 40 ሺህ ሄክታር የሚጠጋ መሬት በመስኖ ስንዴ ልማት የተሸፈነ መሆኑን የገለፁት ዶክተር ይልቃል÷ ይህ ግን በቂ ባለመሆኑ በየደረጃው ያለ ባለድርሻ አካል በቀጣይ ለተሻለ ልማት መስራት ይኖርበታል ሲሉም ተናግረዋል።

በባህርዳር ዘንዘልማ ቀበሌ ኩርቢ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ አርሶአደሮች÷ከዚህ በፊት በአካባቢው የበጋ ስንዴ ልማት ተሞክሮ እንደማያውቅ ገልፀው÷ በኩታ ገጠም እያለሙት ያለው ስንዴ  እንዳስደሰታቸው ነው የተናገሩት።

በሙሉጌታ ደሴ

 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.