የሀገር ውስጥ ዜና

የተቀናጁ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለማስተዋወቅ የሚመክር መድረክ ተዘጋጀ

By Alemayehu Geremew

March 04, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፕሮሞሽን ስትራትቴጂ ላይ የሚመክር መድረክ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ጋር በትብብር አዘጋጅቷል፡፡

መድረኩ የተቀናጁ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለማስተዋወቅ የተዘጋጀ ሲሆን በመርሃ- ግብሩ ላይ ከተለያዩ የመንግስት መሥሪያ ቤቶች የተወጣጡ ባለሙያዎች፣ የሥራ ሃላፊዎች እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተሳታፊዎች ናቸው።

በፕሮሞሽን ስትራቴጂ ዶክመንቱ ላይ የተለያዩ ገለፃዎች እየተደረጉ ሲሆን ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡