Fana: At a Speed of Life!

የሩስያ ጦር በኪየቭ የሚገኘውን በአውሮፓ ትልቁን የኑውክሌር ማብላያ ያዘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩስያ ጦር በደቡብ ምዕራብ ዩክሬን በምትገኘው ዝፖሮዢያ ሌሊቱን ሙሉ ውጊያ ካደረገ በኋላ በአውሮፓ ትልቁ እንደሆነ የሚነገርለትን የኒውክሌር ማብላያ እንደተቆጣጠረ የዩክሬን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡

“በአሁኑ ጊዜ ዝፖሮዢያ በሩሲያ ጦር ተይዛለች” ሲል የሩስያ የኑውክሌር ቁጥጥር ሃላፊ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠቱን ቲ አር ቲ ዘግቧል፡፡

በተያያዘ ዜና የሩስያ መረጃ ቁጥጥር አገልግሎት፥ የ”ቢቢሲ ሩስያ” ፣ “ሬዲዮ ሊበርቲ” እና ሜዱዛ የተሠኙትን መገናኛ ብዙኃን ማገዱን አስታውቋል፡፡

የመገናኛ ብዙሃኑ የሩሲያን የውስጥ ፖለቲካና ደህንነት እየጎዱ በመሆኑ እገዳ መጣሉን ነው ያመለከተው።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.