የሀገር ውስጥ ዜና

የበልግ አብቃይ አካባቢዎች በሚቀጥሉት 10 ቀናት ዝናብ ያገኛሉ

By Feven Bishaw

March 04, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአገሪቷ የበልግ አብቃይ አካባቢዎች በሚቀጥሉት 10 ቀናት ውስጥ ዝናብ እንደሚያገኙ ብሔራዊ የሚቲዮሮሎጂ ኢኒስቲቲዩት አስታወቀ፡፡

ኢኒስቲቲዩት እንዳስታወቀው በተጠቀሱት ቀናት ከኦሮሚያ ክልል ጅማ፣ ኢሉአባቦር፣ ምሥራቅ ወለጋ፣ ከአማራ ክልል ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ምሥራቅ ጎጃም፣ ደቡብ ጎንደር እና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ሁሉም ዞኖች እንዲሁም አዲስ አበባ ዝናብ ያገኛሉ፡፡