Fana: At a Speed of Life!

የኮምቦልቻ ወደብና ተርሚናልን ቀድሞ ወደ ነበረበት አቋም ለመመለስ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መደበኛ አገልግሎት መስጠት የጀመረውን የኮምቦልቻ ወደብና ተርሚናል ቀድሞ ወደ ነበረበት አቋም ለመመለስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሮባ መገርሳ እንደገለጹት÷ ወደቡ በነበረው ጦርነት ውድመት ከደረሰበት በኋላ እንደገና ስራ ለማስጀመር ድርጅቱ በወሰደው አፋጣኝ እርምጃ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

የኮምቦልቻ ወደብና ተርሚናል ከጥር 12 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የደንበኞችን ትዕዛዝ መቀበል መጀመሩ የተገለፀ ሲሆን፥ የተወሰኑ ኮንቴነሮችም ኮምቦልቻ ወደብ ደርሰው መራገፋቸውን አቶ ሮባ ገልጸዋል፡፡

የኮምቦልቻ ወደብና ተርሚናል የገቢና ወጪ ዕቃዎች መዳረሻ ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን፥ ለአካባቢው ኢኮኖሚ ከፍተኛ ፋይዳ ያለው እና ተመራጭ ከመሆኑ አንጻር ደንበኞች በወደቡ የሚያገኙትን አገልግሎት ይበልጥ የተሳለጠ ለማድረግ ጉዳት የደረሰባቸው ደንበኞችን አገልግሎት ቅድሚያ እንዲያገኙ ድርጅቱ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

አያይዘውም ኮምቦልቻ ደረቅ ወደብ ይስተናገዱ የነበሩ የመልቲ ሞዳል ደንበኞች አገልግሎቱን መጠቀም እንዲጀምሩ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.