የሀገር ውስጥ ዜና

የዘይት ፋብሪካዎች የሀገር ውስጥ የዘይት ፍጆታን ይሸፍናሉ የሚል ተስፋ ቢጣልባቸውም ይህንን ማሳካት አልቻሉም

By Feven Bishaw

March 04, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የተቋቋሙ የዘይት ፋብሪካዎች የሀገር ውስጥ የዘይት ፍጆታን ይሸፍናሉ የሚል ተስፋ ቢጣልባቸውም በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ይህንን ማሳካት አልቻሉም፡፡

በዚህም የሀገሪቱን 60 ከመቶ የዘይት አቅርቦት የመሸፈን አቅም እንዳለዉ የተነገረለት የፌቤላ የዘይት ፋብሪካ በውሱን በማምረት ላይ ቢሆንም የኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦት ተግዳሮት እንደሆነበት ያነሳል፡፡