Fana: At a Speed of Life!

በዓለም ባንክ ቀጠናዊ የዲጂታል ትስስር ፕሮጀክት ውስጥ ኢትዮጵያ ተካተተች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ባንክ ቀጠናዊ የዲጂታል ትስስር ፕሮጀክት ውስጥ ኢትዮጵያ እንድትካተት ከስምምነት ተደረሰ።
በዓለም ባንክ የአይሲቲ ፖሊሲ መሪ ዶክተር ቲም ኬሊ የተመራ ቡድን በኢትዮጵያ በዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀክት ስር የሚተገበሩ ስራዎች ያሉበትን ደረጃ እየገመገመ መሆኑ ተገልጿል።
የባንኩ የአይሲቲ ፖሊሲ መሪ እና የኢትዮጵያን የዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀክት የሚከታተሉት ዶክተር ቲም ኬሊ ፕሮጀክቶቹ በተያዘላቸው በጀትና የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ሊከናወኑ እንደሚገባ ምክረ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።
ሱዳንን፣ ደቡብ ሱዳንንና ሶማሊያን ተጠቃሚ ለማድረግ የዓለም ባንክ በሚደግፈው ቀጠናዊ የዲጂታል ፕሮጀክት ውስጥ ኢትዮጵያ መካተት እንደምትችልም ተናግረዋል።
በዚህም ወቅት የዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀክት የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንፎርሜሽን አጀንዳ አንዱ የማስፈፀሚያ ስልት አድርገን እየሰራን ነው ሲሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ በቀጣናዊ የዲጂታል ትስስር ፕሮጀክት ድጋፍ ውስጥ በመካተቷ ያመሰገኑት ሚኒስትር ዴኤታዋ÷ የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት ለሚደረገው ጥረት ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ነው የተናገሩት።
የኢትዮጵያ የዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀክት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚመራ ሲሆን÷ በስሩ በተለያዩ ተቋሟት የሚተገበሩ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑም ተጠቅሷል።
የአለም ባንክ የኢትዮጵያ የዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀክትን በገንዘብ እየደገፈ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን፣ ትምህርት ሚኒስቴር፣ የብሄራዊ የዲጂታል መታወቂያ ኘሮጀክትና የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በፕሮጀክቱ የተካተቱ ተቋማት መሆናቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.