Fana: At a Speed of Life!

የቀድሞው የካፍ ዋና ፀሀፊ አምር ፋህሚ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ዋና ፀሀፊ አምር ፋህሚ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ግብፃዊው አምር ፋህሚ በካንሰር ህመም ህክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው፥ በ36 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ፋህሚ ከፈረንጆቹ 2017 እስከ 2019 ድረስ የካፍ ዋና ፀሃፊ ሆነው ማገልገላቸው ይታወሳል።

ቀደም ባሉት አመታትም ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች ፕሬዚዳንት ሆነው መርተዋል።

ከዚህ ባለፈም የተለያዩ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ውድድሮችን በበላይነት ያስተዳደሩ ሲሆን፥ በቀጣዩ የካፍ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የመወዳደር እቅድ ነበራቸው።

ምንጭ፦ egypttoday.com/

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.