ሰላምና ዕድገት ላይ ትኩረት ያደረገ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደርን አሁናዊ የሰላምና ፀጥታ ጉዳይ እንዲሁም ልማትንና ዕድገትን መሠረት ያደረገ ውይይት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
በጎንደር የሰላም እና ዕድገት ማኅበር እንዲሁም በጎንደር መልሶ ማቋቋምና ልማት ማኅበር አማካኝነት ነው ምክክሩ የሚካሄደው።
በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሂሩት ካሳው፣ የአማራ ልማት ማህበር ስራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ፈንታን ጨምሮ የጎንደር ተወላጆችና ወዳጆች ተገኝተዋል።
በዓለምሰገድ አሳዬ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!