Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለ44ኛው የካራማራ የድል በዓል የእንኳን አደረሰን መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አባቶቻችን ጥቃቅን ልዩነታቸውን እና የግል ህመማቸውን ወደ ጎን ትተው ሀገራችን ነጻነቷ እና ሉዓላዊነቷ ተከብሮ እንድትቆም በአንድነት ታሪክ ሰርተዋል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡
“አንዳንዶቻችን ዳግም እነሱ የሰሩትን ታሪክ ማክበር እንኳን አቅቶን ወደ መንደር ወርደን፣ በጥላቻ ሰክረን የአባቶቻችንን ታላቅ እና ደማቅ ድል እንዲጠለሽ መስራት ተጠምደናል፤ ይህን ማድረግም የታሪክ ተወቃሽ ያደርገናል” ብለዋል።
“ይህን እያደረጋችሁ ያላችሁ አካላት ቆም ብላችሁ እንድታስቡ ያስፈልጋል” ነው ያሉት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባወጡት በመልዕክታቸው።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.