Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል ኃላፊነታቸውን ባልተወጡ 384 አመራሮች ላይ ፖለቲካዊ ውሳኔ ተላለፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልል ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባልተወጡ 384 የፓርቲው አመራሮች ላይ ፖለቲካዊ ውሳኔ መሰጠቱን በብልፅግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
ፖለቲካዊ ውሳኔ ከተላለፈባቸው መካከል 146 ከአመራርነት እንዲነሱ ሲደረግ÷ ለ238ቱ ደግሞ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል ተብሏል።
በክልሉ “ተለውጦ ሀገርን ለመለወጥ” በሚል መሪ ሃሳብ ሲያካሄድ የነበረው የአመራርና አባላት ሥልጠና ተኮር የግምገማ መድረክም መጠናቀቁ ተገልጿል።
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ የመድረኩን መጠናቀቅን አስመልክተው ትናንት ማምሻውን ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።
ለዜጎች ክብር መቆም፤ ጎጠኝነትና ሌብነትን መፀየፍና ማስወገድ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ በመደመር እሳቤ ሀገርንና ህዝብን ማሻገር የብልፅግና ፓርቲ ግብ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡
መድረኩ በአገልግሎት አሰጣጥና በዳተኝነት፣ ግለኝነት፣ ጥቅመኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ስንፍናና ሌሎች መሰል ህዝብን ያማረሩ ችግሮች እንዳሉ በግልፅ ተገምግሟል ብለዋል።
የህዝብን ጥቅም ማስቀረት ሊደረስበት የተወጠነውን የብልፅግና ጉዞ የሚያደናቅፉ በመሆናቸው በአጭሩ ለመቅጨት መወሰኑን አስረድተዋል።
ከፓርቲው ስነ ምግባርና አስተሳሰብ ያፈነገጡ አካሄዶች፣ አስተሳሰቦችና ተግባሮች ፓርቲው ተሸክሞ እንደማይጓዝ ከጋራ መግባባት ላይ መደረሱን በመግለጫቸው ጠቁመዋል።
የብልፅግና ፓርቲ የመደመርና የወንድማማችነት እሴት መሆኑን አቶ አብርሃም በመግለጫቸው በአፅኖት ተናግረዋል።
በገቢዎች፤ በንግድና በመሬት አስተዳደር ዙሪያ የሚስተዋሉ የሌብነት፣ የጉቦኝነትና መሰል ህዝብን ያማረሩ ብልሹ አሰራሮችን ፓርቲው በፍጹም እንደማይታገስም ገልጸዋል።
በዚህም በክልሉ በየደረጃው የሚገኙ 2ሺህ 490 አመራሮች በግልፅ መረጃዎች በመሞገት ጭምር የማጥራት ሥራ መሰራቱንም አመልክተዋል።
“በዚህ መሰረት በተጠቀሱት የመልካም አስተዳደር ችግሮች እጃቸው ያሉባቸው 384 አመራሮች ተለይተው ፖለቲካዊ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል” ብለዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ እንዲቻል የስነምግባር ጉድለታቸውን የሚያጣራ ከዐቃቤ ህግ፣ ከፖሊስና ከሌሎች አካላት የተውጣጣ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ስራ ጀምሯል ብለዋል።
በቀጣይም የፓርቲውን የሥነምግባር እሴቶችና መሰረታዊ መርሆዎችን አክብረው ሕዝብን በቅንነትና በታማኝነት የማያገለግሉ የአመራር አካላት ከፓርቲው ጋር አብረው መጓዝ እንደማይችሉም ማረጋገጣቸውን ነው ኢዜአ የዘገበው።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.