Fana: At a Speed of Life!

ጤና ሚኒስቴር ለጤና ባለሙያዎች የሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና ውጤት ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዘጠኝ ሙያዎች በዲግሪ ለተመረቁ የጤና ባለሙያዎች የሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና ውጤት ይፋ አደረገ፡፡
ሚኒስቴሩ ውጤቱን ይፋ ያደረገው የተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ሙያ ማኅበራት እንዲሁም የጤና ሚኒስቴር ተወካዮች በተገኙበት ነው፡፡
በመርሃ ግብሩ ንግግር ያደረጉትበሚኒስቴሩ የጤና ባለሙያዎች ብቃት ምዘና ፈቃድ ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ አበባው፥ የብቃት ምዘና ፈተናው ከታህሳስ 21-27 /2014 ዓ.ም መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡
አክለውም፥ ይፋ በሚደረገው ውጤት ላይ በመመርኮዝ የታዩትን ጠንካራና ደካማ ጎኖች በመለየት በቀጣይ የሚሰሩ ስራዎች ይሻሻላሉ ብለዋል፡፡
የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከተጀመረ ጀምሮ ከ71 ሺህ በላይ ተፈታኞች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን፥ 32 ሺህ 480 የሚሆኑት የተሰጠውን ፈተና አልፈው የሙያ ፈቃድ ተሰጥቷቸው ወደ ስራ መግባታቸው ተገልጿል፡፡
የብቃት ምዘና ፈተና ውጤት ለማየት http://Hple.moh.gov.et ይህንን ሊንክ መጠቀም ይቻላል መባሉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.