Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ሕዝብ ሀብት የሆነውና በቀድሞ ስሙ ጥረት ዘላቂ የበጎ አድራጎት ተቋም የስም እና የአርማ ለውጥ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ሕዝብ ሀብት የሆነውና ቀድሞ ጥረት ይባል የነበረው የዘላቂ በጎ አድራጎት ተቋም ስሙ “ንጋት” በሚል አዲስ ስያሜ ተተክቷል።

በቀድሞ ስሙ ጥረት በመባል ለ26 ዓመታት ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስራዎችን ሲያከናውን የነበረው ተቋሙ አዲስ አርማ እና ንጋት የሚል አዲስ ስያሜ ተሰጥቶታል።

ስያሜ እና አርማ የመቀየር ሥነ ሥርዓቱም አሁን በባህርዳር ከተማ እየተከናወነ ይገኛል።

 

በመርሀ ግብሩ ተቋሙ ዘርፈ ብዙ የለውጥ አሰራሮችን እየተገበረ መሆኑ የተነገረ ሲሆን÷ በዚህም የ10 ዓመት ፍኖተ ካርታ እና የአምስት ዓመት ስትራቴጂ በማዘጋጀት ወደ ትግበራ እየገባ መሆኑ ነው የተገለጸው።

አዲሱ ስያሜ፣ አርማ እና ” ዘላቂ የልማት መሰረት” የተሰኘው መፈክር የተመረጠውም ተቋሙ እ.ኤ.አ. በ2050 በአፍሪካ ቀዳሚ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ሽግግር የሚያመጣ የዘላቂ በጎ አድራጎት ተቋም ለመሆን ከተነሳበት ግብ አንፃር መሆኑ ተገልጿል።

በንጋት ባለቤትነት 15፣ እና ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር 4 በድምሩ 19 ኩባንያዎች እና 6 ፕሮጀክቶች በስራ ላይ ይገኛሉ።

አሁን ላይም የተቋሙ ጠቅላላ ሀብቱ 13 ቢሊየን ብር መድረሱ ተገልጿል፡፡

በመርሀ ግብሩ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር እና የንጋት ዘላቂ የበጎ አድራጎት ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ አቶ መላኩ አለበል፣ የንጋት ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አምላኩ አስረስ ፣ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬ ፣ የፌደራል እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በለይኩን ዓለም

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.