Fana: At a Speed of Life!

የዳና የኢስላማዊ ትምህርትና ሥልጠና ታሪካዊ ማዕከል አራተኛ ከሊፋ ሼህ አህመድ ኑር ሼህ ሚስባህ ዐረፉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዳና የኢስላማዊ ትምህርትና ሥልጠና ታሪካዊ ማእከል አራተኛ ከሊፋ ሼህ አህመድ ኑር ሼህ ሚስባህ በትናንትናው እለት በ100 ዓመታቸው ማረፋቸውን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ፡፡
 
ሼህ አህመድ ኑር የዳና ሀሪማን ከሶስተኛው ጠባቂ ከሸህ ሙሐመድ ዘይን ህልፈት በኋላ የተረከቡ ሲሆን፥ ለ46 ዓመታት የማዕከሉ መንፈሳዊ አመራር በመሆን መርተዋል፡፡
 
ሼህ አህመድ ኑር ዳናን ለሊቃውንቱ ሰብእና የሚመጥን መልክና ቅርጽ እንዲኖረው በማድረግ፣ የሃይማኖቱን ሊቃውንት የአውቀት ትውፊት እንዲጠበቅ በማድረግ እና የቤተ እምነቱ ቅርሳዊ ሀብት ወደ ቀጣይ ትውልድ እንዲሻገር በማድረግ ትልቅ መንፈሳዊ አስተዋጽኦ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡
 
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር ዶክተር ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ በሺህ አህመድ ኑር ሕልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ ለቤተሰቦቻቸውና ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡
 
የሼህ አህመድ ኑር የቀብር ስርዓት ከዳናና ከመላው ሀገሪቱ በተሰባሰቡ ኡለማዎች፣ የመጅሊስ ተወካዮች፣ ዘመድ አዝማዶችና የመንግስት ተወካዮች በተገኙበት በዛሬው እለት መንደራ ተብሎ በሚታወቀው የዳና ኡለማዎች መካነ መቃብር ተፈጽሟል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.