Fana: At a Speed of Life!

ንግድ ባንክ እስከ መጋቢት 2 መረጃዎችን ወቅታዊ ያላደረጉ ደንበኞች ማንኛውንም የባንክ አገልግሎት እንደማያገኙ አስታወቀ

ንግድ ባንክ እስከ መጋቢት 2 መረጃዎችን ወቅታዊ ያላደረጉ ደንበኞች ማንኛውንም የባንክ አገልግሎት እንደማያገኙ አስታወ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መረጃዎችን ወቅታዊ ያላደረጉ ደንበኞች እስከ አርብ መጋቢት 2 ቀን 2014 ብቻ ወደ ማንኛውም የባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ አስፈላጊውን መረጃ እንዲያሟሉ አሳሰበ፡፡

ባንኩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እ.ኤ.አ በ27/08/2021 ያወጣውን መመሪያ ተከትሎ የደንበኞቹን መረጃ የማደራጀትና የማጥራት ስራ እ.ኤ.አ እስከ የካቲት 27 ቀን 2022 ድረስ መሰራቱ እና በርካታ ደንበኞችም መረጃዎቻችሁን ወቅታዊ ማድረጋቸውን ገልጿል፡፡

ሆኖም እስከ አርብ መጋቢት 2 ቀን 2014 ድርስ መረጃዎችን ያላሟሉ ደንበኞች ሒሳባቸውን ማንቀሳቀስ እንደማይችሉ ባንኩ አስታውቋል፡፡

በዚህም የባንክ ሒሳባቸውን ማንቀሳቀስ የሚችሉት በአካል የባንኩ ቅርንጫፍ በመገኘትና አስፈላጊውን መረጃ በመስጠት ብቻ መሆኑንም ጠቁሟል፡፡

በመሆኑም መረጃዎችን ወቅታዊ ያላደረጉ ደንበኞች ወደ ማንኛውም የባንኩ ቅርንጫፍ እስከ አርብ መጋቢት 2 ቀን 2014 ብቻ በመሄድ አስፈላጊውን መረጃ በመስጠት ሒሳባቸውን ማንቀሳቀስ የሚያስችል መረጃ እንዲሰጡ ባንኩ አሳስቧል፡፡

መረጃዎችን ወቅታዊ ያላደረጉ ደንበኞች ከመጋቢት 2 ቀን በኋላ ማንኛውንም የባንክ አገልግሎት (የሞባይል ባንኪንግ፥ የኢንተርኔት ባንኪንግ እንዲሁም የኤቲኤም እና የፖስ አገልግሎት ጨምሮ) ማግኘት እንደማይችሉ አስታውቋል።­

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.