በመዲናዋ የምግብ ዘይት በድብቅ ይዘው ለማሸሽ የሞከሩ ህገወጦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአዲስ አበባ ለህብረተሰቡ የሚውለውን የምግብ ዘይት በድብቅ ይዘው ለማሸሽ የሞከሩ ህገወጦችን ግብረ-ሃይሉ በቁጥጥር ስር አዋላቸው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማው አለአግባብ የምግብ ፍጆታዎችንና ሌሎች ጥሬ እቃዎችን የሚሸሽጉና የሚያሸሹ ደላሎችንና ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር ግብረ ሃይል አቋቁሞ ወደ ተግባር መግባቱ ይታወቃል፡፡
በዚህም በትናንትናው እለት ለሊቱን ከአዲስ አበባ ለህብረተሰቡ የሚውለውን የምግብ ዘይት በድብቅ ይዘው ለማሸሽ የሞከሩ ህገወጦችን ግብረ-ሃይሉ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ አሁንም ሰፊ ክትትል በማድረግ ህገወጦችን ለህግ እንደሚያቀርብ ማስታወቁን ከከተማው ከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ አሁንም ሰፊ ክትትል በማድረግ ህገወጦችን ለህግ እንደሚያቀርብ አስታውቋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!