Fana: At a Speed of Life!

በቶኪዮ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቶኪዮ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ጠንካራ ተፎካካሪዎች በመሆን አሸናፊ መሆን ችለዋል፡፡
 
በወንዶች የማራቶን ዉድድር ታምራት ቶላ በ2 ሰአት ከ2 ደቂቃ ከ14 ሰከንድ በመግባት 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ሲያጠናቅቅ ሹራ ቂጣታ 5ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል፡፡
 
በሴቶች በተካሄደው ውድድር ደግሞ አሸቴ በከሪ በ2 ሰአት ከ17 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ በመግባት 2ኛ ደረጃን ይዛ ስታጠናቅቅ ጎይተቶም ገብረስላሴ እና ህይዎት ገብረኪዳን 3ኛ እና 5ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን ማጠናቀቃቸውን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.