Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ፑቲን ሃገራቸው ከዩክሬን እና ከውጭ አጋሮች ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆኗን አስታወቁ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሞስኮ ከዩክሬን እና ከውጭ አጋሮች ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆኗን አስታወቁ።
 
ፕሬዚዳንት ፑቲን ከቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን ጋር የስልክ ውይይት አድርገዋል።
 
በዚህ ወቅትም ሃገራቸው ከዩክሬን እና አጋሮች ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ስለመሆኗ መግለጻቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።
 
ቀናትን ባስቆጠረው የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ሁለቱ ሃገራት ከትናንት በስቲያ ለሰላማዊ ዜጎች ሰብአዊ መተለለፊያ ኮሪደር ለማዘጋጀት መስማማታቸው ይታወሳል።
 
አገራቱ እያካሄዱት ካለውጦርነት ጎን ለጎን የሚካሄደው የሰላም ድርድርም ነገ ለሶስተኛ ጊዜ ቀጥሎ እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.