Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ሂሩት ዘመነ በቤልጂየም ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር ሂሩት ዘመነ በቤልጂየም ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር አምባሳደር ፍራንክ ፊሊክስ ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይታቸው ወቅት በኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ለማድረግ፣ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለመፍታት እየተወሰዱ ስላሉ እርምጃዎች ገለጻ አድርገውላቸዋል።
 
መንግስት የአባይን ውሃ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ላይ በመመስረት እና የአፍሪካ ህብረት የሶስትዮሽ ድርድርን በማቀላጠፍ ከታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ጋር በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን አብራርተዋል።
 
አምባሳደር ፊሊክስ በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለው የሰላም እንቅስቃሴዎች ወሳኝነት እንዳላቸው ጠቅሰው፥ ሁሉም ወገኖች ሰብዓዊ አቅርቦትን ተደራሽ ማድረግ እንዳለባቸውም ገልፀዋል።
 
ቤልጂየም ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የረጅም ጊዜ ግንኙነት እንደምታከብር መናገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
 
አምባሳደሮቹ ኢትዮጵያ እና ቤልጀየም በንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ በቱሪዝም እና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ዙሪያ ያላቸውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.