Fana: At a Speed of Life!

የባንግላዴሽ ንግድ ሚኒስትር ቲፑ ሙንሺ የእንጦጦ ፓርክን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በባንግላዴሽ ንግድ ሚኒስትር ቲፑ ሙንሺ የተመራው የልኡካን ቡድን ዛሬ በእንጦጦ ፓርክ ጉብኝት አካሂዷል።
 
የልዑካን ቡድን አባላቱ ፓርኩን በመጎብኘታቸው ደስተኛ መሆናቸው እና ኢትዮጵያ እምቅ የተፈጥሮ ሃብት ያላት አስደናቂ አገር መሆኗን አውስተዋል፡፡
 
አገራቸው በተለያዩ ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር ለመሥራት ዝግጁ እንደሆነችም ነው የገለጹት።
 
የልኡካን ቡድኑ ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ ጋር በመገናኘት ፍሬያማ ውይይት ያካሄዱ ሲሆን÷በመዲናዋ በተካሄደው የኢንቨስትመንት ፎረም ላይም ተሳትፈዋል።
 
የልኡካን ቡድኑ አባላት በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ለተደረገላቸው መልካም አቀባበል እና መስተንግዶ ምስጋናቸውን ማቅረባቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.