Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ሐረርጌ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ87 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር በቁጥጥር ስር ዋለ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ87 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር በቁጥጥር ስር ዋለ።

በዞኑ ቀርሣ ወረዳ በጊዚያዊ የመቆጣጠሪያ ኬላ የካቲት 27 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ በተደረገ ፍተሻ ከአዲስ አበባ ወደ ጅግጅጋ በህዝብ ትራንስፖርት በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 87 ሺህ 311 ዶላር በቁጥጥር ስር መዋሉን ነው ፖሊስ ያስታወቀው።

የዞኑ ፖሊስ የኮሚዩኒኬሽን ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ቶሎስ ጐሹ በተለይም ለፋና ብሮካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥
ተጠርጣሪው ህገወጥ ዶላሮቹን በፈሳሽ የህፃናት ወተት ማሸጊያ ውስጥ አስገብቶ አስመስሎ በማሸግ በዳቦ ቅርጫት ውስጥ ካርቶን ሸፍኖበት ሲያጓጉዝ በፀጥታ ሃይሉ እጅ ከፍንጅ ተይዞ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ተጠርጣሪው ከህገወጥ ዶላሮቹ በተጨማሪ 13 የተለያዩ ባንኮች የሂሳብ ደብተሮች መያዛቸውንም ነው ኢንስፔክተር ቶሎሳ የገለፁት።

በተሾመ ኃይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.