Fana: At a Speed of Life!

በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት የነዳጅ ዋጋ በእጅጉ እየጨመረ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት የነዳጅ ዋጋ ላይ በእጅጉ ጭማሪ መታየቱ ተገለጸ፡፡

አሁን ላይ የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 139 ነጥብ 13 ዶላር ሲሆን፥ ከፈረንጆቹ 2008 አጋማሽ ጀምሮ ከፍተኛ ጭማሪ እንደሆነም ነው የተገለጸው ፡፡

ከነዳጅ በተጨማሪ በሩሲያ የሚመረቱ እንደ ስንዴ እና ብረት ያሉ ምርቶች ላይም ከፍ ያለ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል ነው የተባለው፡፡

ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ የወርቅ ዋጋ እስከ 2 ሺህ 86 ዶላር ድረስ ማሽቆልቆሉ ተሰምቷል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም የዶላር ምንዛሬ ከፍተኛ ጭማሬ ማሳየቱም ነው የተነሳው፡፡

የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎችም የነዳጅ ድፍድፍ ዋጋ መጨመር ጋር ተያይዞ ጥንቃቄ መውሰድ እንደሚገባ ይመክራሉ፡፡

በዓለም አቀፉ ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ከወዲሁ እየታየ ሲሆን፥ በተለይም የአውሮፓ አክሲዮን ገበያ መጎዳቱን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ከ2020 አጋማሽ ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ዩሮ ከ1 ነጥብ 10 ዶላር በታች ምንዛሬ ተቀምጦለታል፡፡

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት በሳምንቱ መጨረሻ በሩሲያ ላይ የተጣለው ማዕቀብ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ “ከባድ ተጽእኖ” እንደሚፈጥር ማስጠንቀቁን ቲ አር ቲ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.