Fana: At a Speed of Life!

በሽብርተኛው ቡድን ወረራ የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀያቸው የመመለሱ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል-የአማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሽብርተኛው ቡድን ወረራ የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀያቸው የመመለሱ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን የአማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር እያሱ መስፍን ገልጸዋል፡፡

በአሸባሪው ሸኔ ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ ወገኖችም በአብዛኛው በመጠለያ ጣቢያ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይም በአሸባሪው ቡድን ወረራና ከተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ በክልሉ ከ11 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ወገኖች የዕለት ምግብ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ነው ያሉት፡፡

ለእነዚህ ወገኖች በአንድ ወር ብቻ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን ኩንታል በላይ እህል እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡

እስካሁን በማኅበረሰቡ፣ በግል ድርጅቶች እና ረጂ ድርጅቶች ይቀርብ የነበረው የምግብ ድጋፍ ወደ አንድ ቋት በማስገባት እየቀረበ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ 70 በመቶውን የፌደራሉ መንግሥት 30 በመቶውን ደግሞ የክልሉ መንግሥት እየሸፈነ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም ማኅበረሰቡ በመጠለያ ጣቢያዎች ለተጠለሉ ተፈናቃዮች ምግብ እና ምግብ ነክ ቁሳቁስ እያቀረበ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ ህብረተሰቡ ይህን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.