Fana: At a Speed of Life!

ጂቡቲ የገቢ ጭነቶች ከወደቦቿ በፍጥነት ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ በትብብር ለመሥራት ተስማማች

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጅቡቲ የኢትዮጵያ ገቢ ጭነቶች ከወደቧ እና ነጻ ቀጣናዎች ወደተለያዩ የኢትዮጵያ መዳረሻዎች በፍጥነት ለማጓጓዝ በትኩረት ለመሥራት መስማማቷ ተገለጸ፡፡
በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ ከጅቡቲ ወደቦች እና ነጻ ቀጣናዎች ባለሥልጣን ሊቀመንበር አቡበከር ዑመር ሃዲ ጋር በጅቡቲ ዓለምአቀፍ ነጻ የንግድ ቀጣና ላይ ተወያይተዋል፡፡
በበርካታ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት መደረጉን እና ስምምነት ላይ መደረሱን ነው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላከተው፡፡
÷ ኢትዮጵያን ከጅቡቲ ወደብ የሚያገናኘውን እና እየተገነባ ያለውን የጋላሞ – ሞሉድ የአስፋልት መንገድ ማፋጠን እና በአስቸኳይ አጠናቆ ወደ ሥራ ማስገባት እንደሚገባም ሁለቱ ወገኖች ተስማምተዋል፡፡
የጋላሞ – ሞሉድ የአስፋልት መንገድ ÷ ከኢትዮጵያ እስከ ጂቡቲ ወደቦች የተዘረጋ እንደሆነና እጅግ የተጨናነቀ ኮሪደር መሆኑም የተጠቆመ ሲሆን ፣ኢትዮጵያ በባሕር የምታስገባውን ከፍተኛ ጭነት በዋናነት ለማመላለስ የምትጠቀምበት አውራ ጎዳና መሆኑም ተገልጿል፡፡
ጂቡቲ የኢትዮጵያ ገቢ ጭነቶች ለረጅም ጊዜ ወደብ ላይ እንዳይቆዩ፣ በአነስተኛ ወጪ እና ፍጥነት ተጓጉዘውም ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ በትብብር እንደምትሠራ ፣ ብሎም የመንገድ ላይ መጓተቶች እንደሚቀረፉ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.