Fana: At a Speed of Life!

ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ስርዓቶች ለሀገራዊ የሰላም ግንባታ ውጥኖች የጎላ ሚና አላቸው – ሰላም ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ስርዓቶች ለሀገራዊ የሰላም ግንባታ ውጥኖች የጎላ ሚና እንዳላቸው የሰላም ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላም ለማስፈንና ግጭቶችን ለመፍታት ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ስርዓቶችን ከሳይንሳዊው የግጭት አፈታት ጽንሰ ሀሳብ ጋር በማገናዘብ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚያግዝ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡
እንደ ሀገር አለመግባባቶች ወይም ግጭቶች የሚፈቱበት እምቅ ማህበራዊና ሀገር በቀል የግጭት መፍቻ ስርዓቶች እንዳሉ በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን መኮንን ተናግረዋል፡፡
የራስ የሆኑ መለያ ጸጋዎችን በመዘንጋትና የውጭውን ዓለም ተጽዕኖ በሙሉ እንደ ስልጣኔ በመውሰድ የራስ መገለጫ የሆኑ ማህበራዊ ሀብቶችን ባለመጠቀም እንደ ህዝብ ዋጋ እየተከፈለ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡
ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ስርዓቶችን በማጠናከርና አለመግባባቶችን በሰላማዊ ውይይት በመፍታት፣ የሽምግልና እና የእርቅ ስርዓቶችን በማጎልበት የኢትዮጵያን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ የበኩላችንን ድርሻ መወጣት ይገባናልም ብለዋል፡፡
መድረኩ ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓቶችን ከሳይንሳዊው የግጭት አፈታት ጋር አጣጥሞ በመጠቀም ካሉ የሽምግልና ክህሎቶች ላይ ተጨማሪ አቅም በመፍጠር የመፈጸም አቅምን ለማጎልበት ያለመ መሆኑን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በመድረኩ ላይ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ኡጋዞች፣ አባገዳዎች፣ ሱልጣኖች እና ሀደሲንቄዎች ተሳትፈዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.