Fana: At a Speed of Life!

በቻይና ሁቤይ ግዛት በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ 311 ኢትዮጵያውያን በኮሮና ቫይረስ እንዳልተጠቁ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቻይና ሁቤይ ግዛት በሚገኙ 24 ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ 311 ኢትዮጵያውያን እስካሁን በኮሮና ቫይረስ እንዳልተጠቁ ተገለፀ።

በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ባወጣው መረጃ በውሃን እና ሌሎች ከተሞች በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች በቫይረሱ አልተጠቁም ብሏል።

ኤምባሲው ለእረፍት በኢትዮጵያ የሚገኙ በቻይና የሚማሩ ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲያቸው ጋር ግንኙነታቸውን እንዲቀጥሉም አሳስቧል።

ሆኖም ተጨማሪ መረጃ ይፋ እስከሚሆን ድረስ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዎቻቸው እንዳይመለሱም ነው ያለው ኤምባሲው።

በሀገሪቱ ለሚገኙ ተማሪዎች ከቫይረሱ ራሳቸውን መከላከል እንዲችሉ የማስክ እና ሌሎች ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው ተብሏል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.