በጉለሌ ክፍለ ከተማ በአራት መጋዘን ያለአግባብ የተከማቸ የምግብ ዘይት ተያዘ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ጉለሌ ክፍለ ከተማ በአራት መጋዘን ያለአግባብ የተከማቸ የምግብ ዘይት በተቋቋመው ግብረሃይል ተያዘ፡፡
የኑሮ ውድነት እንዲባባስ ሰው ሰራሽ የዋጋ ውድነት በመፍጠርና ምርቶችን በመደበቅ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ህገወጥ ደላሎችንና ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ግብረ ሃይል አቋቁሞ ወደ ተግባር መግባቱ ይታወሳል፡፡
በዚህ መሰረት ግብረሃይሉ እያደረገ ባለው ቁጥጥር በዛሬው እለት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ስሙ ሙሉጌታ መናፈሻ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በህብረተሰቡ ጥቆማ በአራት መጋዘን ውስጥ የተከማቸ የምግብ ዘይት መያዙን ከአዲስ አበባ ከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በቀጣይም ቁጥጥሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የተገለጸ ሲሆን÷ የከተማዋ ነዋሪዎች ጥቆማዎችን በማቅረብ የጋራ ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!