Fana: At a Speed of Life!

ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ከ39 ሺህ ቶን በላይ የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ39 ሺህ ቶን በላይ የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

የግብርና ሚኒስቴርና የፌደራል ቡናና ሻይ ባለስልጣን በደቡብ ምዕራብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ተገኝተው የቡና እደሳ ስራን ተመልክተዋል፡፡
የክልሉ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዳይሬክተር አቶ አስራት መኩሪያ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በሀገሪቱ ቡና፣ ቅመማ ቅመምና ሻይ ለማምረት ከፍተኛ አቅም ያለው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ክልሉ 541 ሺህ 141 ሄክታር ቡና ማምረት የሚችል አቅም ያለው ሲሆን እስከ አሁን 300 ሺህ ሄክታር ገደማ የሚሆነው በቡና የተሸፈነ መሆኑን ጠቁመዋል።

በ2014 በጀት ዓመት 61 ሺህ 864 ቶን የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እስካሁን ከ39 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለገበያ መቅረቡንም ነው የተናገሩት።

በዘንድሮው አመት ለማዕከላዊ ገበያ ከቀረበው ቡና 20 ሺህ ቶን የሚሆነው ከቤንች ሸኮ ዞን መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

በተስፋየ ምሬሳ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.