Fana: At a Speed of Life!

ፓኪስታን የምዕራባውያን “ባሪያ” አይደለችም- ጠ/ሚ ኢምራን ካህን

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፓኪስታን የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ የ22 አገራት ዲፕሎማቶች ሩሲያ በዩክሬን ላይ እየወሰደች ያለውን ወታደራዊ እርምጃ እንድታወግዝ ያቀረቡትን ጥሪ ውድቅ አድርጋለች፡፡
 
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በቅርቡ ሩሲያ በዩክሬን ላይ እያካሄደች ያለውን ወታደራዊ እርምጃ ለማውገዝ ጠቅላላ ጉባኤ ማካሄዱ ይታወሳል፡፡
 
በዚህም ፓኪስታን ድርጊቱን ለማውገዝ በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ድምጸ ተዓቅቦ ማድረጓን ተከትሎ የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ የ22 አገራት ዲፕሎማቶች ባወጡት የጋራ መግለጫ ፓኪስታን ÷ ሩሲያ በዩክሬን ላይ እየወሰደች ያለውን ወታደራዊ እርምጃ እንድታወግዝ ጠይቀዋል።
 
የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካህን ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ÷ “ዲፕሎማቶች ያቀረቡት ጥሪ ያልተለመደ ዲፕሎማሲያዊ አካሄድ ከመሆኑ ባሻገር የአንድን አገር ሉዓላዊነት የሚጥስ ነው” ሲሉ አጣጥለውታል፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ማሳሰቢያውን የሰጡት አገራት÷ ፓኪስታን የእነሱ ባሪያ እና ተላላኪ ናት ብለው ያስባሉን? እነሱ የሚፈልጉትን ሁሉ የምናደርግ ይመስላቸዋል?” ሲሉም ጠይቀዋል፡፡
 
አያይዘውም “ዲፕሎማቶቹ በጉባኤው በተመሳሳይ መልኩ በውሳኔ ሃሳቡ ላይ ድምጸ ተዓቅቦ ላደረገችው ህንድ ለምን የማሳሰቢያ መግለጫ አላወጡም” ሲሉም? ነው የጠየቁት።
 
ፓኪስታን አውሮፓውያን በአፍጋኒስታን የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ጦርን ሲያሰማሩ ድጋፍ በመስጠቷ በርካታ ጉዳቶችን አስተናግዳለች፤ለዚህ ግን ከምስጋና ይልቅ ትችት የደረሰባት መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውሰዋል፡፡
 
ፓኪስታን÷ ከሩሲያ፣ አሜሪካ፣ ቻይና እንዲሁም ከአውሮፓ አገራት ጋር ጥሩ ግንኙነት ያላት መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ አገራቸው በጉዳዩ ላይ ገለልተኛ መሆኗንም አስረድተዋል፡፡
 
ምንጭ፦ ሬውተርስ
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.