ስፓርት

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአዳማ ከተማ አቻ ተለያየ

By Tibebu Kebede

February 24, 2020

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት ብቸኛ ጨዋታ ዛሬ ተካሂዷል።

የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአዳማ ከተማ በአዲስ አበባ ስታዲየም ያደረጉት ጨዋታ ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች ፋሲል ከነማ እና መቐለ 70 እንደርታ መሸነፋቸው ይታወሳል።

ፕሪሚየር ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ28 ነጥብ ሲመራ ፋሲል ከነማ በ26፣ መቐለ 70 እንደርታ በ25 ነጥቦች ይከተላሉ።

ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና ደግሞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision