Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ አካባቢዎች በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 59 በርሜል ነዳጅ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ አካባቢዎች በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 59 በርሜል ነዳጅ መያዙ ተገለፀ፡፡

በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 26 በርሜል ነዳጅ መያዙን የጋምቤላ ክልል አስታወቀ፡፡

የክልሉ የንግዱ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ኦኬሎ ኡቦንግ እንደገለጹት÷ በተደረገው ክትትል አንድ ግለሰብ በጋምቤላ ከተማ ከሚገኘው ታፍ ማደያ በሕገ ወጥ መንገድ ነዳጅ በመቅዳት ወደ አኮቦ ለመውሰድ ሲንቀሳቀስ በሕግ ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ግለሰቡ ንግድ ፈቃድ እንደሌለውና ለመንግሥት ግብር እንደማይከፍል ጠቅሰው÷ በሀገሪቱ በወጣው ሕግና ደንብ መሰረት ተገቢው እርምጃ እንደሚወሰድበት መግለጻቸውን ከጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በክልሉ የነዳጅ ስርጭት ቁጥጥር ላይ እና በከተማው በአላቂ እቃዎች ላይ የሚስተዋለውን የዋጋ ጭማሪ ለማረጋጋት ቢሮው በትኩረት እየሠራ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡

በተመሳሳይ በባሌ ዞን ጋሰራ ወረዳ ሕገወጥ 33 በርሜል ነዳጅ በቁጥጥር ስር መዋሉን የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት መግለፁን ከባሌ ዞን ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.