Fana: At a Speed of Life!

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር የፊታችን እሁድ ይፈፀማል

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር የፊታችን እሁድ ይፈፀማል ።

የሥርዓተ ቀብር አስፈጻሚ ዐቢይ ኮሚቴ ዛሬ በጠቅላይ ቤተክህነት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ÷ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት የአቡነ መርቆሬዎስን ስርዓተ ቀብር ለማስፈፀም 12 አባላት ያሉት ዐቢይ ኮሚቴ እና በስሩም 12 ንዑስ አባላት ያሉት ኮሚቴ ተቋቁሞ እየሰራ መሆኑ የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ፀሀፊ አቡነ ዮሴፍ ተናግረዋል ።

በዚህ መሰረት ÷የፊታችን መጋቢት 3 አስከሬናቸው ካረፈበት በሞተር ታጅቦ ወደመስቀል አደባባይ የሚያመራና በዚያም የሽኝት መርሀግብር የሚደረግለት ሲሆን የተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ ስርዓቶችም ይከናወናሉ ተብሏል።

እሁድ መጋቢት 4 ቀንም በቅድስት ስላሴ ካቴድራል አስከሬናቸው በክብር ያርፋል ።

በጸጋየ የወንድወሰን

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.