Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ከ11 ቢሊየን ብር በላይ ከወለድ ነፃ የብድር አገልግሎት ሰጠ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ከ11 ቢሊየን ብር በላይ ከወለድ ነፃ ብድር ለተጠቃሚዎች ማሰራጨቱን አስታወቀ፡፡

የባንኩ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ጎዳና ቃበታ÷ ካለፉት ሰባት ዓመታት ወዲህ አገልግሎቱን የሚሰጡ ቅርንጫፎችን በማስፋፋት በአሁኑ ወቅት ከ2 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ደንበኞችን ማፍራት መቻሉን ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ 13 ባንኮች ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ያነሱት አቶ ጎዳና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ከደንበኞቹ ከ13 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ በማሰባሰብ ከ1 ሺህ 5 በላይ ለሚሆኑ ደንበኞቹ ከ11 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ገንዘብ ከወለድ ነፃ በሆነ መልኩ ማሰራጨቱን ገልጸዋል፡፡

ከእምነትና ከወለድ ጋር በተያያዘም የባንክ አገልግሎት ላላገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በየአካባቢው አገልግሎቱን የሚሰጡ ቅርንጫፎችን በመክፈት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለመሆንም በትኩረት እየሰራ ይገኛል ተብሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ 13 የንግድ ባንኮች ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት እየሰጡ ሲሆን የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ከ1 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑት ደንበኞቹ ብድር በማቅረብ ግንባር ቀደም መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተሾመ ኃይሉ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.