ሊባኖስ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የቆየ ግንኙነት ከፍ አድርጋ እንደምትመለከት ገለጸች
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሊባኖስ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የቆየ ግንኙነት ከፍ አድርጋ እንደምትመለከት የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ናጂብ አዝሚ ሚካቲ ገለጹ፡፡
የኢትዮጵያ ቆንስል ጄኔራል አቶ ተመስገን ዑመር ከሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ናጂብ አዝሚ ሚካቲ ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ፣ በቀጣናዊ ጉዳዮች እና የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።
በውይይቱ አቶ ተመስገን ዑመር በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፥ ለሰላም የተደረጉ እንቅስቃሴዎች እና ሁሉን ዓቀፍ ውይይት፣ የሰብዓዊ አገልግሎት ተደራሽነት እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አስመልክቶ የተወሰዱ እርምጃዎችን አንስተውላቸዋል።
ሊባኖስ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የረዥም ጊዜ ግንኙነት ከፍ አድርጋ እንደምትመለከተው መግለጻቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!