Fana: At a Speed of Life!

5ኛው ዙር የኦዳ አዋርድ ሽልማት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 5ኛው ዙር የኦዳ ሽልማት ስነ ስርዓት በሸራተን አዲስ ሆቴል ተካሄደ፡፡
በስነ ስርዓቱ በሙዚቃ፣ ፊልም እና ሥነ ጽሑፍ ዘውጎች ከ60 በላይ የሚሆኑ አርቲስቶች በዕጩነት ቀርበዋል፡፡
በ20 የተለያዩ ዘርፎች ሽልማቱ የተዘጋጁ ሲሆን÷ ከእነዚህ ውስጥ ስምንቱ በሙዚቃ፣ ሰባቱ በፊልም እንዲሁም ሁለቱ ደግሞ በሥነ ጽሑፍ ዘርፎች የተዘጋጁ ናቸው፡፡
በ5ኛው ዙር የኦዳ ሽልማት ከአፋን ኦሮሞ በተጨማሪ በሲዳምኛ እና አፋርኛ ቋንቋች የተዘጋጁ ሥራዎች ለዕጩነት መቅረባቸው ተመላክቷል፡፡
የኦዳ ሽልማት በበሻቱ ቶላማርያም መልቲሚዲያ ተዘጋጅቶ ከኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በትብብር በየዓመቱ የሚካሄድ ዝግጅት ነው፡፡
በሙዚቃ ዘርፍ የ2013 የኦዳ አዋርድ የሴቶችን ሽልማት መርጊቱ ወርቅነህ አሸንፋለች፡፡
በዘመድኩን ምስጋናው
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.