Fana: At a Speed of Life!

የብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ ፓርቲው በአደረጃጀት ጠንክሮ የሚወጣበት ይሆናል- ዶክተር ዓለሙ ስሜ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ ፓርቲውን በብቃት የሚመሩ የሥራ ሀላፊዎች የሚመረጡበት እና ፓርቲውም ጭምር በአደረጃጀት ጠንክሮ የሚወጣብት እንደሚሆን የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ዶክተር አለሙ ስሜ ተናግረዋል።
ከፋና ወቅታዊ ጋር ቆይታ ያደረጉት ዶክተር አለሙ ስሜ÷ አሁን ላይ ፓርቲው በብዙ ስኬቶች እና ፈተናዎች ውስጥ ሆኖ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቆ የጉባኤውን እለት እየተጠባበቀ መሆኑን ገልጸዋል።
ፓርቲው ለ3 ቀናት በሚያካሂደው ጉባኤ የተለያዩ አቅጣጫዎችን ከማስቀመጥ ባለፈ የተለያዩ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ነው ያሉት።
ከዚህ ባለፈም ፓርቲው የሚያስቀምጣቸውን እና የሚወስናቸውን ውሳኔዎች በሚገባ ማስፈፀም የሚችሉ ትክክለኛ እና ታማኝ መሪዎችን በመለየት ይመርጣልም ነው ያሉት፡፡
ከጠቅላላ ጉባኤው በኋላም ፓርቲው የመረጠውን ህዝብ ለማገልገል ካለፈው ስህተቱ በመማር እና ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል በዋናነት በነገ ላይ ትኩረት አድርጎ በልዩነት፣ በአደረጃጀት እና በአስተሳሰብ ጠንክሮ ይወጣልም ነው ያሉት ስራ አስፈፃሚው::
በአዲሱ ሙሉነህ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.