Fana: At a Speed of Life!

የሸገር ዳቦ ምርት ከነገ ጀምሮ ለገበያ መቅረብ ይጀምራል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዋጋ ጭማሪና በኑሮ ውድነት ላይ ያለውን ጫና ለመቀነስ የምግብ ፍጆታዎች ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።
በተለይም በከተማ አስተዳደሩ በመንግስት ድጎማ እየተሰራጨ ያለውን የምግብ ዘይትና ዳቦ በተመለከተ ልዩ ትኩረት ሰጥተናል ብለዋል ከንቲባዋ።
የምግብ ዘይት በህገወጥ ክምችት የተገኘውን ጨምሮ በተለያዩ አቅራቢዎች እንዲቀርብ በማድረግ ለጊዜው ከ2 ሚሊየን ሊትር በላይ ዘይት እየተሰራጨ መሆኑንም ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።
በመሆኑም የከተማዋ ነዋሪ በተለይም በዝቅተኛ ገቢ የሚተተዳደሩ በየአካባቢያቸው ወደሚገኙ የሸማች ሱቆች በመሄድ ምርቶቹን ማግኘት እንደሚችሉም አስታውቀዋል።
የሸገር ዳቦን በተመለከተም ፋብሪካው በእድሳትና በወቅቱ የስንዴ ዋጋ ንረት ምክንያት ለጊዜው ማምረት አቁሞ እንደነበር ገልፀዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ለሸገር ዳቦ 613 ሚሊየን ብር ድጎማ በማድረግ እንዲሁም በ198 ሚሊየን ብር ለስንዴ አቅርቦት በድምሩ 812 ሚሊየን ብር በመመደብ የዳቦ ምርት ማስጀመር ችሏልም ነው ያሉት፡፡
ከነገ ጀምሮም ምርቱ ወደ ገበያ የሚወጣ በመሆኑ ህብረተሰቡ የሸገር ዳቦ በሚሰራጭባቸው ማዕከላት ዳቦ ማግኘት እንደሚችልም ነው የገለጹት።

ነገር ግን እነዚህ ምርቶች ዝቅተኛውንና በተለይም ቅድሚያ ወደሚሰጠው ህዝብ በሚፈለገው ደረጃ መድረስ ላይ እጥረቶች እንዳሉ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አንስተዋል፡፡

ይህንንም ለመቅረፍም የከተማ አስተዳደሩ የጀመረው ቁጥጥር ቢኖርም በተለይም የዳቦ በመንግስት ከፍተኛ ድጎማ እየቀረበ ሳለ የተሻለ ገቢ ያላቸው የንግድ ድርጅቶችና ባለሃብቶች ምርቱን ወስደው የሚያተርፉበት ሁኔታ እንዳለ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ህብረተሰቡ ይህንን ሁኔታ በመጠቆም፣ በማጋለጥ፣ በመቆጣጠር በኩል ድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቀርበው ከተማው የንግዱ ማህበረሰብም በመተሳሰብ ለጊዜው ትርፍ ቀንሰው ህዝቡን እንዲያተርፉ ጠይቀዋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.