በአፋር ክልል የኮማሚ-ጋላእሉ የጠጠር መንገድ ግንባታ በተያዘለት ዕቅድ እየተካሄደ መሆኑ ተመላከተ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የገቢ-ረሱ እና የሀሪ ረሱ ዞኖችን የሚያገናኘው የኮማሚ-ጋላእሉ የጠጠር መንገድ ግንባታ አፈጻጸም በተያዘለት ጊዜ እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የአፋር ክልል የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ደረሳ አሊ÷ ፕሮጀክቱ በአፋር ክልል እያከናወነ ያለውን የገቢ-ረሱ እና የሀሪ ረሱ ሁለት ዞኖችን የሚያገናኘውን የኮማሚ-ጋላእሉ የጠጠር መንገድ ግንባታ አፈጻጸም ጎብኝተዋል፡፡
አቶ ደረሳ አሊ በጉብኝታቸው ወቅት እንደገለጹት÷ 57 ነጥብ 3 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የመንገድ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ እየተከናወነ ነው፡፡
መንገዱ የሁለቱን ዞኖች አርብቶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች የገበያ ትስስና የእርስ በእርስ ግንኙነት ሊያጠናክር በሚችልበት ሁኔታ እየተገነባ ነው ማታቸውን ከአፋር ክልል የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!