Fana: At a Speed of Life!

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት አባላት ከአስተዳደሩ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አባላት ከአስተዳደሩ ነዋሪዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በድሬዳዋ ውይይት አካሄዱ።

በውይይት መድረኩ ከተለያዩ የከተማዋ ቀበሌዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች መገኘታቸውን ከድሬዳዋ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ነዋሪዎች በተለያዩ ወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች፥ በከተማዋ በሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና የልማት ጥያቄዎች ላይ አስተያየቶችን የሰጡ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

ነዋሪዎቹ በሰጡት አስተያየት በከተማዋ ያለውን የሥራ አጥነት ችግር ለመቀነስ ይቻል ዘንድ አስተዳደሩ በሥራ እድል ፈጠራ ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በከተማው ያጋጠመውን ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ንረት ለመፍታት በህገወጥ መንገድ ለመክበር አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ መንግስት እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባም ጠይቀዋል።

በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች የሚሰሩ መንገዶች ብዙም ሳይቆዩ እየፈረሱ ነው ያሉት ነዋሪዎቹ ÷ የከተማዋ መንገድ ላይ ያሉ የመብራት ፖሎች ተጠግነው አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶክተር ቢፍቱ መሃመድ÷ በአስተዳደሩ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና የተለያዩ የልማት ጥያቄዎችን ለመፍታት በቀጣይ አስተዳደሩ ከነዋሪው ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ አመላክተዋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.