Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ እና ጃፓን በጥር ወር ከፍተኛ የንግድ ጉድለት አጋጠማቸው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ እና ጃፓን በጥር ወር ከፍተኛ የንግድ ጉድለት እንዳጋጠማቸው ተገለጸ፡፡

አሜሪካ ከፍተኛ ነው የተባለለትን የንግድ ዋጋ ጉድለት ያስመዘገበችው የገቢ ንግዷ በመጨመሩ እና የወጪ ንግዷ በመቀነሱ መሆኑን የሀገሪቷ ንግድ ሚኒስቴር ማክሰኞ ዕለት ባወጣው ሪፖርት አመላክቷል፡፡

እንደ ሪፖርቱ የአሜሪካ ገቢ ንግድ በ1 ነጥብ 2 በመቶ የጨመረ ሲሆን ወጪ ንግዷ ደግሞ በ1 ነጥብ 7 በመቶ አሽቆልቁሏል፡፡

አሜሪካ በጥር ወር የ314 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ገቢ ንግድ ስትፈጽም ፣ 224 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር የሚያወጡ ምርቶቿን ደግሞ መላኳን ነው ሪፖርቱ ያመለከተው፡፡

የሀገሪቷ የምርት እና የአገልግሎት ጉድለት ከታሕሣሥ ወር አንጻር ሲቃኝ በ9 ነጥብ 4 በመቶ መውደቁን ሲ ጂ ቲ ኤን ሺንዋን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

በተመሣሣይ ጃፓን በሥምንት ዓመታት የንግድ ሥርዓቷ አስመዝግባ የማታውቀውን የንግድ ጉድለት በጥር ወር ማስመዝገቧን ነው ሬውተርስ የዘገበው፡፡

ጃፓን የንግድ ክፍተቱ ያጋጠማት የኃይል አቅርቦት ዋጋ በመጨመሩ እና ፋብሪካዎቿ የኃይል አቅርቦቶቻቸውን ከውጭ ለመሸፈን በፈጸሟቸው ግዢዎች መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ሀገሪቷ ወደ ውጭ የምትልካቸው ተሽከርካሪዎች በቁጥር ማሽቆልቆላቸውን የዜና ምንጩ አመላክቷል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.