Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ሀገራት ሩሲያ እና ህዝቦቿን ሊያከብሩ ይገባል – ፕሬዚዳንት ማክሮን

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2014አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት በሰላም እንዲፈታ ከተፈለገ የአውሮፓ ሃገራት ሩሲያን እና ህዝቦቿን ሊያከብሩ እንደሚገባ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አሳሰቡ፡፡
 
ፕሬዚዳንቱ በቅድመ ምርጫ ስብሰባ ላይ በተደረገ ውይይት ላይ እንደተናገሩት÷ ከሩሲያ እና ከቤላሩስ ማህበረሰቦች ጋር በተለያዩ ዘርፎች ላይ በጋራ እየሰሩ እና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይም እየተነጋገሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
 
የሃገራቱን ህዝቦች ግንኙነት ማጠናከር የሁላችንም ሃላፊነት ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ÷ለዚህም ከሩሲያ እና ቤላሩስ አርቲስቶች እና ምሁራን ጋር በተለያ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
 
በተመሳሳይ ምንም እንኳን ልዩነቶች ቢኖሩም ከአገራቱ መሪዎችጋር መነጋገራቸውን እንደሚቀጥሉ እና ፈረንሳይ ሁልጊዜም ሩሲያን እና ህዝቦቿን እንደምታከብርም አጽንኦጽ ት ሰጥተዋል፡፡
 
የዩክሬኑን ቀውስ ለማርገብም ሩሲያ እና ህዝቦቿ በአክብሮት ሊያዙ ይገባል ያሉት ፕሬዚዳንት ማክሮን÷ያለ ሩሲያ ተሳትፎ በቀጠናው ዘላቂ ሰላም ማስፈን አስቸጋሪ መሆኑን አብራርተዋል ፡፡
ሩሲያ ከሁለት ሳምንት በፊት የዩክሬን ወታደሮችን ጥቃት ለመከላከል ከዶኔስክ እና ሉሃንስክ ህዝቦች ሪፐብሊክ ለቀረበላቸው የእርዳታ ጥሪ ምላሽ በመስጠት ዩክሬን ላይ ወታደራዊ ዘመቻ መጀመሯ ይታወሳል፡፡
 
የሩሲያን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ተከትሎም በአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት ውስጥ በሚገኙ የሩሲያ ዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች ፣ ድርጅቶች እና ዜጎች ላይ ጥቃቶች እየደረሱ መሆኑ ተመላክቷል።
 
በተጨማሪም የሩሲያ ዜጎችን የማግለል እና ጥቃት የማድረስ አዝማሚያ በአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት ህዝቦች እና ፖለቲከኞች እየተስተዋለ መሆኑን ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.